መግቢያ
ባንዴራ የአንድ ሃገር መለያ ብቻ ሳይሆን መገለጫ መመኪያ እና እናት አገር ብለን እምንሞትላት የተለያዩ ቀለማት የተሸከመች ትእምርት ናት ፡፡ ባንዴራ የብሄር ብሄረሰቦች አንድነት ፤ ነፃነት፤ እድገት፤ ልማት፤ ፍቅርና ሰላም የተሸከመች ምልክታችን ናት፡፡ ይህቺ ባንዴራችን በህገመንግስቱ የሰፈረች ማንም ሊቀይራት እና ሊክዳት የማይገባ ብዙ ሺ ኢትዮጵያውያን የሞቱላት አርማችን ናት::
ሰንደቅ አላማ የህዝቦች ሉዓላዊነትና በመፈቃቀድ ላይ
የተመሰረተ የአንድነት መገለጫ ነው፡፡ ለዚህ ነው በተለያየ የአለማችን ክፍሎች የሚገኙ ሃገራት የራሳቸውን ምልክት ሰንደቅ
የክብራቸው የአንድነታቸው የማንነታቸው መገለጫ አድርገው የሚወስዱት፡፡ እንደ ኢዮጵያ ላለች ባለ 3000 አመት ታሪካዊ ሃገርና
ከ85 በላይ ብሄር ብሄረሰብና ህዝብ ለሚኖርባት ሃገር ደግሞ ባንድራ ልዩ ትርጉም አለው፡፡ሰንደቅ አላማችን በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ መለያና የኢትዮጵያ ብሄሮች እና ህዝቦች ባህል ቋንቋ እና ሀይማኖት እና የአስተሳሰብ ልዩነት የያዘ ነው፡፡በሰንደቅ አላማችን ጥላ ስር ተሰባስበን ለህገ መንግስቱና ለህገ መንግሰታዊ ስርዓተ ማበብ የቆየውን አብሮ የመቻቻል ባህላችን ለማጎልበት የህዳሴ ጉዞችን አውን ለማድረግ ያለንን ዝግጅት ዳግም ቃል በመግባት የምናድስበት ነው፡፡
ተማሪዎችና መምህራን የዚች አገር የወደፊት ዕጣ ፋንታ የምትወሰኑ እንደመሆናችሁ መጠን አሁን ላለነው ትውልዶች ከባድ ጠላት የሆነውን ድህነትን ታግሎ ለመጣል በሰንደቅ አላማ ስር ተሰባስባችሁ ለህዳሴ ጉዞችን አውን መሆን ከመቼውም ጊዜ በላይ መረባረብ የኖርባችኋል፡፡
የጽሁፉ ዓላማ
ለ7ኛ ጊዜ የሚከበረውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን ምክኒያት በማድረግ
Ø
የኢፌድሪ ሰንደቅ ዓላማ እሴቶችን ከእሴቶቹ
በስተጀርባ ያለውን ሃገራዊ ክብርና ምንነት ለማስረጽ
Ø
በዚህ ዓመት የሚጠናቀቁ የሃገራችን የእድገትና
የትራንሰፎርሜሽን እቅድና የምዕተ አመቱን የልማት ግቦች በት/ቤታችን በላቀ ሁኔታ ለመፈጸም ትስስር ለመፍጠር
Ø
ተማሪዎችና መምህራን ለሰንደቅ አላማችን
ያለንን ፍቅርና ክብር የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ ሃገራዊ ግደታችን እንድንወጣ አይነተኛ መሳሪያ አድርገን እንድንሄድ የሚያስችል
መግባባትና ተነሳሽነት ለመፍጠር
Ø
ተማሪዎችና መምህራን ሃገራቸውን ባንድራ
ታሪካዊ አመጣት ተገንዝበው በሃገራቸው እንድኮሩ ለማድረግ
Ø
ተማሪዎችና መምህራን ስለ ባንድራ ምንነትና
አከባበር ግንዛቤ እንድኖራወቸው ለማድረግ
የሰንደቅ አላማ በዓል መሪ ቃል
በድህነት ላይ በከፈተችው ዘመቻ ብሄራዊ ክብሯንና ሰንደቅ አላማዋን ከፍ እያደረገች ያለች ሃገር!!!
በበዓሉ ወቅት ሊተላለፉ የሚገባቸው መልዕክቶች
v
አድሱ ብሄራዊ አርበኝነት ድህነትን በልማት
ማሸነፍ ነው!!
v
ሰንደቅ አላማችን የዘላቂ ሰላማችን ምልክት
ነው!!
v
ሰንደቅ ዓላችን የእኩልነታችን የብዙህነታችን
የዴሞክራሲያዊ አንድነታችን መገለጫ ነው!!
v
ድህነትን በመዋጋት ብሄራዊ ክብራችንና
ሰንደቅ አላማችንን እያከበርን ነው!!
v
ከዚህ ደርሰናል ቀሪ ጉዞአችን በህዝብ
ተሳትፎ ይሳካል!!
v
ታሪክ ከመዘከር ታሪክ ወደ መስራት ተሸጋግረናል!!
v
ሰንደቅ አላማችንና የህዳሴው ግድባችን
ብሄራዊ ኩራታችን ናቸው!!
የሰንደቅአላማችንታሪካዊአመጣጥዳሰሳ
በየዘመናቱም በአገራችን መሪ ሄዶ መሪ ሲተካ፣ በሰንደቅ ዓላማው የተለያዩ አርማዎችን ሲቀርጹበት ታይቷል። እንግዲያውስ የኢትዮጵያ ሰንደቅ-ዓላማ ታሪካዊ ኣመጣጡና የኅብረ-ቀለማቱ ትርጉም ከኣፈታሪክ ያገኘነውና ከአበው የተማርነውን ከዚህ ቀጥለን ለመግለጽ እንሞክራለን።
ወደ ኣምስት መቶ ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊትም፣ ቀዳማዊ ምኒልክ የጽላተ-ሙሴ ታቦትን ይዞ አክሱም ሲገባ፣ ኢትዮጵያም የሕገ ኦሪትን ስርዓት ስትቀበል፤ "ሃገራችን የእግዚአብሔር ብርሃን በራላት" ተብሎ ከአረንጓዴው በላይ የብጫ ቀለም "ብርሃን" እንደኣከሉበት አፈ-ታሪኩ ይነግረናል። ኣሁንም የሸማን ጨርቅ ወይባ በተባለው፣ ብጫ ቀለም ባለው ቅጠል ቀጥቅጠው በመንከር ነበር የሠሩት። (ዛሬም ቢሆን በወይባ ቅጠል ጭማቂ የተነከረ ልብሰ-መነኰሳት ብጫ ቀለም አለው።) እነዚህም ሁለት ቀለማት እስከ ኣብርሃ ወኣጽብሓ ዘመነ መንግሥት፤ ኢትዮጵያም የክርስትና ሃይማኖትን እስከ ተቀበለችበት ዘመን ድረስ የሃገራችን ሰንደቅ-ዓላማ ሆነው፣ ለብዙ ዘመናት ጸንተው ቆይተዋል።
በሦስት መቶ ሠላሳ ዓመተ-ምሕረት (ከክርስቶስ ልደት በኋላ) አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ክርስትናን በኢትዮጵያ በሰበኩ ደግሞ፣ "ወንጌል የኦሪት ፍሬ ነው፣ በክርስቶስ መስቀልና ደምም የተገኘ ነው" በማለት፣ ከሁለቱ ቀለማት በላይ ቀይ ቀለም ጨምረው፣ ሰንደቅ-ዓላማውን ሦስት ኅብር፣ ማለትም አረንጓዴ፣ብጫና፣ቀይኣደረጉት።
ከአበው ቅድመ አያቶቻችን የሰማነውና የተማርነው የሰንደቅ ዓላማ ጥንታዊ አመጣጥ አፈ-ታሪክ ባጭሩ ይኸው ሲሆን፤ ታሪኩ ግን በዚህ አያበቃም። በየዘመናቱ ሰንደቅ ዓላማችን በልዩ ልዩ ንጉሠ ነገሥትና መሪ፣ በመሳፍንትም ዘመን ምን ዓይነት ሁኔታዎች አሳልፋ ይሆን?
ሰንደቅ-ዓላማችንም በዚሁ መልኳ ለብዙ ዘመናት ቆይታለች። ሰንደቅ-ዓላማ "ንጉሠ-ነገሥት ዘኢትዮጵያ" ተብሎ የነገሥታት ሁሉ ንጉሥ በመሆን ከነገሠው ብቻ ስትገኝ፣ ሌሎች ከበታቹ ያሉት ተራ ንጉሦች ግን የየራሳቸውን ይዘው፣ የሸዋ፣ የጐጃም፣ የትግሬ፣ የወሎ... ንጉሥ ተብለው ይጠሩ ነበር እንጂ "ኢትዮጵያ" ኣይባሉም። ኢትዮጵያ የሚባለው በሊቀ-ጳጳሳት የሚቀባው ንጉሠ-ነገሥቱ ብቻ ነበር። ሌሎች ንጉሦችም የየራሳቸው የሆኑ ልዩ-ልዩ ሰንደቅ ዓላማዎችና የተለያዩ አርማውችም ሊኖሯቸው ይችላሉ። በየዘመናቱም ኣንዳንዱ ንጉሠ-ነገሥት አርማውን በሰንደቅ-ዓላማ ላይ ሲያትም፣ ሌላውም ይህ አልበቃ ሲለው፣ ኅብረ-ቀለማቱን የላዩን ወደ ታች፣ የታቹን ወደ ላይ ሲገለብጥ፣ የሚቀጥለውም ንጉሥ መልሶ ሲያቀናው፣ እንዲህ እያለ ዘመናትን አሳልፋለች፡ ዐፄ ኃይለሥላሴ በነገሡ ጊዜ "የቅጠል ልምላሜ ከስር፣ የኣበባና የብርሃን ቀለም ብጫው ቀጥሎ፣ ከሁሉ በላይ ደግሞ ቀይ፣ የፍሬ ምልክት" መሆን ይገባል ብለው ሲገልጹላቸው፣ ንጉሡም በነገሩ ተስማሙበት። የኅብረ ቀለማቱ ስርዓትም እንዲታረም ቢሞክሩ፣ ቦሊቭያ (Bolivia) የተባለች የደቡብ አሜሪካ አገር ቀድማ ይህንኑ የኅብረ-ቀለማት በተባበሩት መንግሥታት ኣስመዝግባለች ስለ ተባለ፣ "ማስተካከሉ ብዙ ችግር አለበት..." ተብሎ፣ ሰንደቅ ዓላማው ሳይታረም የታቹ ላይ፣ የላዩ ታች፣ ተዘቅዝቆ ቀረ።
ኣንዳንድ ዘመናውያን ጸሓፊዎች ግን የሃገር ሽማግሎችና በሃገር ውስጥ የቆየውን ጥንታዊ ኣፈ-ታሪክ ኣጠያይቀው ሳይመረምሩ፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም ያለውን የሰንደቅ ዓላማ ጥንታዊነት ማስረጃ ሳይገነዘቡ፣ "ኢትዮጵያ ባንዴራም አርማም አልነበራትም፣ ባንዴራ የዘመን አመጣሽ፣ እንዲያውም ከፖርቱጊዞችና ቱርኮች ወዲህ የመጣ ነው..." የሚሉ አይጠፉም። ጥንታዊትዋ ኢትዮጵያ ግን የሸማ ጨርቅ ቀለም ነክሮ በዘንግ ማንጠልጠል ይቅርና፣ ከኣፈር ንጥር ኣንጥራ የወርቅ፣ የብርና፣ የነሓስ (Bronz) ብሮችና ሳንቲሞችም እንደነበሯት ታሪክ ይመሰክራል። እንደ ዛሬው በየሕንፃውና በየኣውራ ጐዳናው፣ በየእለቱም ባንዴራ የማውለብለብ ልማድ አይኑር እንጂ፤ ሰንደቅ-ዓላማ የሚባል ፈጽሞ አልነበረም ማለት ትክክል አይመስለንም። ለምሳሌ አርማ ይጠቀሙ እንደነበር የሚያሳይ በአክሱም ሓወልት ጫፉ ላይ፣ ከበስተጀርባው፣ ክብ የሆነ የጋሻ አርማ መሳይ ቅርጽ በግልጽ ይታያል።
ከታች ያሉ ታሪካዊ የኢ/ያ ባንዴራዎች ማንም ኢትዮጵያዊ ያውቃቸዋል ብዬ እገምታለሁኝ፡፡ ነገር ግን እኔ ማሳየት የፈለኩት ዐላማቸው ነው፡፡ በተለይ በተራ ቁጥር 6 ያለው ባንዴራ በሽግግር መንግስት ለ6 ዓመታት ያገለገለ ነው፡፡ ይህ ባንዴራ በደርግ ጊዜም የነበረ ነው፡፡ ልዩነቱ የመጠን ብቻ ነው፡፡ ታድያ የድሮ ናፋቂዎች ይህን ዐላማ የሌለው ባንዴራ በአሁን ጊዜም ስያውለበልቡት ይታይል፡፡ በተለይ በውጭ አገር የሚገኙት የደርግ ትርፍራፊና ድያስፖራ ነን ባዮች የድሮውን ስርዓት ሲናፍቃቸው ይታያል፡፡ አሁን ያለው የኢ/ያ ሰንድቅ ዓላማ የራሱ ትርጉም አለው፡፡ አረንጓዴው የአገር ልማት፣ ብጫው ሰላምና ተስፋ፣ ቀይው የኢ/ያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የከፈሉት መስዋእትነት ያመለክታል፡፡ ሰማያዊ መደቡ ሰላምን ኮኮቡ ብዛኃነትና አንድነትን ጨረሩ ደግሞ ዕድገትን ያሳያል፡፡ አሁን እነዚህ ሐይሎች ይህንን ነው የማይቀበሉት፤ ብዛኃነታችንና አንድነታችንን፣ ዕድገታችንን ነው የማይቀበሉት፡፡ የኢ/ያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች እውቅና ማግኘታቸው ያንገበግባቿል፡፡ የድሮውኑን በመናፈቅ ብሄር ብሀረሰቦችና ህዝቦች እንደ ድሮው ተጨቁነው እንዲኖሩ ይፈልጋሉ፡፡ የኢ/ያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የመንነታቸውን መለያ የሆነውን ሰንደቅ ዐላማ ለማንቋሸሽ ይሞክራሉ፡፡ እነዚህ ፀረ ብሄር ብሄረሰቦች በቅርብ ቀን በአሜሪካ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ትክክለኛውን የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ያለአግባብ ስያዎርዱ የሚናፍቁትን የድሮውን ስርዓት ስጠቀምበት የነበረው ባንዴራ ለመስቀል ሲሞክሩ ታይቷል፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን እነዚህ የአገር ፍቅር የሌላቸው ሐይሎች ለልጆቻቸው እያወረሱት ያለውን ጉዳይ ምንድነው? በሰሩት በኢትዮጵያ ህዝብ በፈፀሙት ግፍና ወንጀል ወደዚች አገር መመለስ እንደማይችሉ በመገንዘባቸው የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንደሚባለው በየስበስባው እንደ ውሻ መጮህ ተያይዞታል፡፡ እኛ ግን ሰባተኛው የሰንደቅ ዐላማ ቀን በመጪው ዛሬ ጥቅምት 3 ቀን 2007ዓ/ም በድምቀት እናከብራለን፤“በህዝቦች ተሳትፎና ትጋት ድህነትን ድል በመንሳት ብሔራዊ ክብርና ሰንደቅ ዓላማዋን ከፍ ከፍ በማድረግ ላይ ያለች አገር ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል፡፡
የተለያየ አርማና ሰንደቅ-ዓላማ በየክፍለ ሃገራቱ መኖር በሌሎችም ሃገሮች የተለመደ ነው። ለምሳሌ በአሜሪካን አገር እያንዳንዱ ክፍለ ሃገር (State) ካሊፎርንያ፣ አሪዞና፣ ቴክሳስ... የየራሳቸው የሆነ ባንዴራና አርማ ብቻ ሳይሆን፣ የየራሳቸው የሆነ እንስሳ፣ ወፍ፣ ቢራቢሮ... ወዘተ. አሏቸው። በአንድነት "አሜሪካ" ሲባሉ ግን የ51 ከዋክብትና፣ የቀይና ነጭ ሰረዝ የሆነው ሰንደቅ ዓላማቸው የአንድነታቸው ምልክት ነው።
ለኛም እነዚህ አረንጓዴ፣ ብጫ፣ ቀይ፣ ኅብረ-ቀለማት ክርስትያን፣ እስላም ሳይባል፣ የመላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕብረትና ኣንድነት ምልክት ናቸው። በዓለምም ሁሉ የኢትዮጵያ ሰንደቅ-ዓላማ መሆናቸው ተጋንነው የታወቁት ጣልያን ኢትዮጵያን ደግማ በወረረችበት ዘመን ነው። አሁን በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በብዙ ኣህጉሮች፣ በተለይ በምእራባዊው ዓለም በልብስ፣ በቆብ፣ በሌላም ቆሳቁስት ላይ እያተሙ በባንዴራችን ሲያጌጡ ይታያል። ብዙውን ጊዜ ይህ ጌጥ የጭቁኖች የተቃውሞ ምልክት መሆኑ ይታወቃል። ያን ጊዜ ኢትዮጵያ በሓያሉ የፋሺስት መዳፍ ስር ወድቃ ብትጠቃም፣ ተዋግታ ማሸነፏ፣ ነፃነቷንም ከአምስት ዓመታት የመራራ ትግል በኋላ መልሳ ማግኘቷ፣ ለዓለም ጭቁኖች ሁሉ ይኽ ታሪኳ ታላቅ ተስፋ ሆኗቸው፣ በትግላቸውም ሁሉ ጽናትና ብርታት ሰጪ ነው።
እነዚህ ሦስቱ ኅብረ-ቀለማት የኢትዮጵያ ሕዝብ የነፃነት ምልክት ናቸው። ዛሬም በፌዴራላዊው ዘመን ያው በድሮ ጊዜ እያንዳንዱ ክፍለ ሃገር የየራሱ ባንዴራ እንደነበረው፣ ልዩ-ልዩ ሕዝቦች፣ ክፍለ-ሃገሮችና አህጉሮች የየራሳቸው የሆነ ሰንደቅ ዓላማና አርማ ቢኖራቸውም ቅሉ፣ ለጦርነት ሲወጡ ግን በዚህች ሰንደቅ ዓላማ ስር ተባብረው በመዝመት ለኣነድነታቸውና ትብብራቸው ምልክት የሆነች ይህች ሰንደቅ ዓላማ ናት። ከዚያም ታልፎ በዓለም ሃገራት ሁሉ በየኤምባሲውና በየሰልፉ ሸንጐ፣ በኦሌምፒክና በሌላም የስፖርት መድረኮች ስትታይ ይህች ሰንደቅ ዓላማ ለሁሉ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ታሪካዊ ቅርስና የኩራት ምንጭ ሆና ለዘልዓለም ስትውለበለብ ትኖራለች።
ለኛም እነዚህ አረንጓዴ፣ ብጫ፣ ቀይ፣ ኅብረ-ቀለማት ክርስትያን፣ እስላም ሳይባል፣ የመላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕብረትና ኣንድነት ምልክት ናቸው። በዓለምም ሁሉ የኢትዮጵያ ሰንደቅ-ዓላማ መሆናቸው ተጋንነው የታወቁት ጣልያን ኢትዮጵያን ደግማ በወረረችበት ዘመን ነው። አሁን በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በብዙ ኣህጉሮች፣ በተለይ በምእራባዊው ዓለም በልብስ፣ በቆብ፣ በሌላም ቆሳቁስት ላይ እያተሙ በባንዴራችን ሲያጌጡ ይታያል። ብዙውን ጊዜ ይህ ጌጥ የጭቁኖች የተቃውሞ ምልክት መሆኑ ይታወቃል። ያን ጊዜ ኢትዮጵያ በሓያሉ የፋሺስት መዳፍ ስር ወድቃ ብትጠቃም፣ ተዋግታ ማሸነፏ፣ ነፃነቷንም ከአምስት ዓመታት የመራራ ትግል በኋላ መልሳ ማግኘቷ፣ ለዓለም ጭቁኖች ሁሉ ይኽ ታሪኳ ታላቅ ተስፋ ሆኗቸው፣ በትግላቸውም ሁሉ ጽናትና ብርታት ሰጪ ነው።
እነዚህ ሦስቱ ኅብረ-ቀለማት የኢትዮጵያ ሕዝብ የነፃነት ምልክት ናቸው። ዛሬም በፌዴራላዊው ዘመን ያው በድሮ ጊዜ እያንዳንዱ ክፍለ ሃገር የየራሱ ባንዴራ እንደነበረው፣ ልዩ-ልዩ ሕዝቦች፣ ክፍለ-ሃገሮችና አህጉሮች የየራሳቸው የሆነ ሰንደቅ ዓላማና አርማ ቢኖራቸውም ቅሉ፣ ለጦርነት ሲወጡ ግን በዚህች ሰንደቅ ዓላማ ስር ተባብረው በመዝመት ለኣነድነታቸውና ትብብራቸው ምልክት የሆነች ይህች ሰንደቅ ዓላማ ናት። ከዚያም ታልፎ በዓለም ሃገራት ሁሉ በየኤምባሲውና በየሰልፉ ሸንጐ፣ በኦሌምፒክና በሌላም የስፖርት መድረኮች ስትታይ ይህች ሰንደቅ ዓላማ ለሁሉ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ታሪካዊ ቅርስና የኩራት ምንጭ ሆና ለዘልዓለም ስትውለበለብ ትኖራለች።
የሰንደቅ አላማችን ምንነትና ቅርጽ
ሰንደቅ አላማ የህዝቦች ሉዓላዊነትና በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ
የአንድነት መገለጫ ነው፡፡
ሰንደቅ አላማችን የተለያዩ ቀለማት ውቅር መሆኗ
ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት ሰንደቅ አላማው ከላይ አረንጓዴ፤ መሃል ቢጫ ከታች ቀይ ሆኖ በክብ ሰማያዊ መደብ ላይ የተቀረጸ
ብሄራዊ ዓርማ ይኖረዋል፡፡ዓርማው በሰንደቅ ዓላማው መሃል ላይ የሚያርፈው የክቡ ዙሪያ የአረንጓዴውና የቀዩን ቀለማት ቁመት
አጋማሽ አክሎ ይሆናል፡፡ እነዚህ ቀለማትም ብሩህና መሰረታዊ መሆን እንዳለባቸውና ቀለማቱም አግድም የተዋቀሩ ና እኩል ስፋት
የሚኖራቸው ሆነው የሰንደቅ አላማው ወርድ የቁመቱ እጥፍ መሆን እንዳለበት በድንጋጌ ተቀምጠዋል፡፡
ከሰንደቅ አላማው መሃል ላይ የሚኖረው አርማም ቅርጹ ክብ
ሆኖ በሰማያዊ መደብ ላይ የሚቀመጥ ሲሆን ከየአቅጣጫው መጥተው የሚገናኙ ቀጥታና እኩል የሆኑ ቢጫ መስመሮች አሉት፡፡ ከዘህም
በተጨማሪ ቀጥታና እኩል ከሆኑ መስመሮች የተዋቀረ ኮከብ ይኖረዋል፡፡በሌላ መልኩም ቀጥታና እኩል በሆኑ መስመሮች መተላለፊያ ላይ
የሚፈነጥቅ ቢጫ ጨረር አለው፡፡
የሰንደቅ አላማችን ቀለማት ትርጉም
ሰንደቅ አላማችን የተወቀረበት ቀለማት በዋናነት 3 ሲሆኑ የእነዚህም ትርጉም
1. አረንጓዴው ስራ የልምላሜና የእድገት ምልክት
2. ቢጫው የተስፋ የፍትህና የእኩልነት
3. ቀይ የነጻነትና ለእኩልነት መስፈን የሚደረግ የመስዋዕትነት የጀግንነት ምልክት ነው፡፡
የሰንደቅ አላማችን ዓርማ ትርጉም
ክብ የሆነው ሰማያዊ መደብ ሰላምን ያመለክታል፡፡ ቀጥታና እኩል የሆኑት መስመሮች የብሄር ብሄረሰቦች
ብሄረሰቦችና የህዝቦች እንድሁም የሃይማኖቶች እኩልነትያመለክታሉ፡፡ቀጥታና እኩል ከሆኑተ መስመሮች የተዋቀረው ኮከብ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች በመፈቃቀድ
የመሰረቱትን አንድነት ያመለክታል፡፡ ቢጫው ጨረር በመፈቃቀድ አንድነት ለመሰረቱት ብሄር ብሄረሰቦች የፈነጠቀው ብሩህ ተስፋ ያመለክታል፡፡
የሰንደቅ ዓላማ መጠን አጠቃቀም
በአዋጅ ቁጥር 654/2009 በተደነገገው መሰረት በተለያየ ቦታና ጊዜ የሚሰቀሉ የሰንደቅ ዓላማ መጠን
የተለያዩ ናቸው፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆኑ ነጥቦችን ለማንሳት ያክል፡-
ü
በከፍተኛ አደባባይ የሚሰቀል የሰንደቅ
አላማ መጠን 210 በ420 ሴንቲሜትር
ü
በመካከለኛ አደባባይ የሚሰቀል የሰንደቅ አላማ መጠን 150 በ300 ሴንቲሜትር
ü
በመስሪያ ቤቶች በከፍተኛ የትምህርት
ተቋማትና ድርጅቶች አደባባይ የሰንደቅ አላማው መጠን 135 በ270 ሴንቲ ሜትር
ü
በትልልቅ የመንግስት ህንጻዎች ላይ የሚሰቀል
የሰንደቅ አላማ መጠን 135 በ270 ሴ.ሜ
ü
በትልልቅ ህንጻዎች ምድር ቤት ውስጥ
የሚገኙ ድርጅቶችና ንግድ ቤቶች የሰንደቅ አላማው መጠን 105 በ210 ሴንቲ ሜትር
ü
በከፍኛ መርከቦችላይና በሰልፍ ጊዜ በክብር ዘብ የሚዘው የሰንደቅ አላማ
መጠን 105 በ210 ሴንቲ ሜትር
ü
ለውጭ ሃገር እንግዳ አቀባበልና ለበዓላት
በየመንገዱ ለሚውለበለቡ የሰንደቅ አላማ መጠን 90 በ180 ሴንቲ ሜትር
ü
በመካከለኛ መርከቦች ላይ የሰንደቅ አላማ
መጠን 90 በ180 ሴንቲ ሜትር
ü
በፕሬዝዳንቱ በጠ/ሚኒስተሩና በአምባሳደሮች
ጽ/ቤት ጠረንጴዛ ላይ የሰንደቅ አላማ መጠን 21 በ42 ሴንቲ ሜትር
ü
ፕሬዝዳንቱ ጠቅላይ ሚኒስተሩና አምባሳደሮች
በሚጓዙበት መኪና ላይ የሚውለበለብ ሰንደቅ አላማ የቁመቱና የወርዱ ቅንብር 3 በ4 ሆኖ 30 በ40 ሴንቲ ሜትር መሆን አለበት፡፡
የሰንደቅ አላማ አሰቃቀል ስርዓት
ሰንደቅ አላማችን በስርዓትና በክብር መሰቀል እንዳለበት ለማንኛውም ኢትዮጰያዊ ግልጽ ነው፡፡ ነገር
ግን ይህ ትክክለኛው የሰንደቅ አላማ አሰቃቀል ምን እንደሆኑ በትክክል የሚያውቀው ሰው በጣት የሚቆጠር ነው፡፡ በመሆኑም ይህን ካለማወቅ
የምናከናውነውን የሰንደቅ አላማ አሰቃቀል ስህተት ለማስተካከል ያስችል ዘንድ ግንዛቤ ሊፈጥሩ የሚችሉ አንዳንድ ነገሮችን ማንሳት
አስፈላጊ ነው፡፡ በመሆኑም ሃገራችን ሰንደቅ አላማን እንደት አድርገን መስቀልና መቼና የት ቦታ ምን አይነት ሰንደቅ አላማ መስቀል
እንዳለብን የሚያሳይ የህግ ማዕቀፍ በአዋጅ አውጥታለች፡፡ የተወሰኑትን ለማየት ያህል፡-
በመጀመሪያ የሰንደቅ አላማውን መውለብለብ የሚያግድ ከአቅም በላይ የሆነ ምክኒያት ካላጋጠመ በስተቀር
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከላይ እስከታች ባሉ የክልል የስልጣን አካላት ጽ/ቤቶች በሚኒስተር መስሪያ
ቤቶች፤ በፍርድ ቤቶች፤ በትምህርት ቤቶች፤ በመከላከያ ድርጅቶች በፖሊስና በጠረፍ ጥበቃ ተቋሞች በሪፐብሊኩ ኢምባሲዎችና በአምባሳደሮች
መኖሪያ ቤት ህንጻዎች እንድሁም የሪፐበሊኩ ንግድ መርከቦችና ጀልባዎች በየቀኑ ሰንደቅ አላማ መሰቀል አለበት፡፡ከዚህ ውጭ ያሉ መስሪያ
ቤቶች በብሄራወ ቀናት ሰንደቅ አላማን ይሰቅላሉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ሰንደቅ አላማ የሚሰቀልበትንና የሚወርድበትን ጊዜ ማወቅ አስፈላጊ በመሆኑ ማንኛውም
ተቋማት ላይ ባንድራ መሰቀል ያለበት ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ነው፡፡ ሆኖም ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀበት አካባቢ የሚገኙ
የመከላከያ ክፍሎች ሁኔታው እስካልተለወጠ ድረስ መደበኛውን ሰዓት ጠብቅ ማውረድና መስቀል አይገደዱም፡፡ በትምርት ቤት ደረጃም ቢሆን
ሰንደቅ አላማው የሚሰቀለው ጠዋት ተማሪዎች ተሰልፈው ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ይሆናል፤የሚወርደው ግን ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
በሌላ መልኩ የሪፐብሊኩ ሰንደቅ አላማ ከክልል ሰንደቅ አላማ ጋር በሚሰቀልበት ጊዜ የፌደራሉ ሰንደቅ
አላማ በስተቀኝ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ከሁለት የክልል ሰንደቅ አላማ ጋር በሚሰቀልበት ጊዜ የፌደራሉ ሰንደቅ አላማ
ከመሃል ሆኖ ከክልሎቹ ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ መሰቀል አለበት፡፡ በሌላ ሁኔታ የፌደራሉ ከብዙ የክልል ሰንደቅ አላማ ጋር በሚሰቀልበት
ወቅት የፌደራሉ ሰንደቅ አላማ በስተቀኝ መጨረሻ ሲውል እሱን ተከትሎ የክልሎች ሰንደቅ አላማዎች በክልሎቹ ስያሜና በአማርኛ ፊደል
ቅደም ተከተል ቦታቸውን በመያዝ መሰቀል አለባቸው፡፡ ከዘሁ ጋር በተያያዘ የፌደራሉ ሰንደቅ አላማ ከሌሎች ሃገራት ሰንደቅ አላማዎች
ጋር በሚሰቀልበት ወቅት በስተቀኝ ይውለበለባል፡፡
በተሸከርካሪዎች ላይ ስለሚኖር የሰንደቅ
አላማ አጠቃቀም
ማንኛውም የውጭ ሃገር ባለስልጣን ወይም የአለም አቀፍ ወይም አህጉር አቀፍ ድርጅት የስራ ኃላፊ ኢትዮጵያ
ውስጥ በሚመጣበት ጊዜ የኢትዮጵያ መንግስት በሚመድብለት ተሸከርካሪ የሚጓዝ ከሆነ በማንኛውም ጊዜ በተሽከርካሪው በስተቀኝ የሪፐብሊኩ
ሰንደቅ አላማ የሚቀመጥ ሲሆን በስተግራ በኩል ደግሞ ባለስልጣኑ ወይም ኃላፊው የተወከለበት ሃገር ወይም ተቋም ሰንደቅ አላማ ይቀመጣል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስተር እንድሁም አምባሳደሮች የሚጓዙበት ተሸከርካሪ
ባቡር አውሮፕላን መርከብ ወይም ጀልባ ላይ ሰንደቅ አላማው ይሰቀላል፡፡በአጠቃላይ የፌደራል ባንድራን በተሸከርካሪ መስቀል የሚችሉት፡-
Ø
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤና
ምክትል አፈጉባኤ
Ø
ፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤና ምክትል
አፈጉባኤ
Ø
ፌደራል መንግስት ሚኒስትሮች
Ø
የሃገሪቱ የቶር ሃይሎች ኤታማዦር ሹም
Ø
የፌደራል ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶች
Ø
የክልል መንግስታት ፕሬዝዳንቶች
ከሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ የተከለከሉ
ተግባራት
እንደ ሃገራችን ነባራዊ ሁኔታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተግባራት መፈጸም የተከለከለ ነው፡፡
v
ሰንደቅ አላማውን አርማውን ሳያካትቱ
መስቀል
v
ሰንደቅ አላማው ላይ ቃላት በመጻፍ ሌሎች
ምልቶችን ወይም አርማዎችን ስዕሎችን ለጥፎ መገልገል
v
ያረጁ የተበላሹ ቀለማቸው የደበዘዙና
ተቀደዱ ሰንደቅ አላማችን መጠቀም
v
ሰንደቅ አላማው በወጣበት ሰንደቅ (ምሰሶ)
ላይ ማስታወቂያ መለጠፍ
v
ህዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ሰንደቅ አላማውን
መድፈር ማዋረድ ወይም ጉዳት እንድደርስበት ማድረግ
v
የሰንደቅ አላማውን ቀለማት ቅደም ተከተል
እንድሁም የብሄራዊ አርማውን መጠን ሳይጠብቁ ማዘጋጀትና መገልገል
v
ሰንደቅ አላማው በአዋጅ ከተጠቀሰው የማውረጃ
ጊዜ በላይ ማቆየት
v
በስብሰባ ወይም በማንኛው መሰል ክንውን
ሰንደቅ አላማን የጠረንጴዛ ሽፋን አድርጎ መጠቀም
v
ሰንደቅ አላማን የህንጻ ወይም የሌሎች
ቁሳቁስ መሸፈኛ ማድረረግ
v
ሰንደቅ አላማን በማንኛውም ንግድ ማስታወቂያነት
መጠቀም
v
ሰንደቅ አላማው በሚወጣበትና በሚወርድበት
ወቅት ተገቢወን ክብር አለመስጠት
በአጠቃላይ ከላይ የተዘረዘሩትን ክንዋኔዎች በሚያከናውን ግለሰብም ሆነ ድርጅት እስከ 3 ሺህ ብር ወይም
አንድ ዓመት በሚያደርስ ጽኑ እስራት ያስቀጣል፡፡
የውይይት መነሻ ነጥቦች
1. የሰንደቅ አላማችን ክብር በአጠቀላይ ተማሪዎቻችንና የአካባቢው ማህበረሰብ እንደት መሳደግ እንችላለን
2. በዚህ በዓል ተንተርሰን የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ከመምህራንና ተማሪዎች ምን ይጠበቃል
3. በቀጣይ ተማሪዎች የሰንደቅ አላማን ክብር
አውቀው በድስፕሊን የታነጹ ሁነው እንድሄዱ ለማድረግ በት/ቤታችን ምን መሰራት አለበት
No comments:
Post a Comment