Wednesday, June 17, 2015

የ2007 ክረምት እቀድ

መግቢያ
የትምህርት ስራ በደቃዎች የተከፋፈለና የሠዓትን ጥቅም ከሚጠበቀው በላይ የተረዳ ስራ ነው፡፡ ለዚህም ነው እያንዳንዱ የትምህርት ስራ በስትራቴጂክ እቅድ ፤ በዓመታዊ እቅድ፤ በወርሃዊ ተግባራት፤ በ15 ቀን ተግባራት ፤ በሳምንት ተግባራት፤ በዕለት ተግባራት ፤ በክፍለ ጊዜ ተግባራት እና በደቂቃዎች ተግባራት ተከፋፍሎ የሚሰጠው፡፡ በዚህም የተነሳ አንድ ተቋም ስራዎችን በዚህ የሰዓት ክፍፍል ስርዓት ከፋፍሎ ማቀድና የታቀደውን መተግበር ይጠበቅበታል፡፡ ከላይ ከተገለፀው የሰዓት ክፍፍል ና የተግባር ዓይነቶች በተጨማሪ አንድን እቅድ በዝግጅት ምዕራፍ፤ በተግባር ምዕራፍና በማጠቃለያ ምዕራፍ በመከፋፈል መስራት ለስራዎች ስኬታማነት የላቀ ሚና አለው፡፡ በመሆኑም የላልይበላ የመ/ደ/ሚ/ሳ/ት/ቤት የ2008ዓ.ም የትምህርት ስራ አመርቂና በውጤት የታጀበ እንድሆን በዝግጅት ምዕራፍ ወይም በክረምት ወቅት ግብዓት ማሟለትና ሎሎች ተግባራትን ማከናወን የሚያስችለውን የግብዓት እቅድ አቅዷል፡፡


የእቅዱ አላማ
v  ለ2008ዓ.ም የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ቀድሞ በማሟላት የትምህርት ዘመኑን የስራ እንቅስቃሴ በውጤት የታጀበ እንድሆን ማድረግ
v  ቀጥታ ለተማሪዎች የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በማሟላት የትምህርት ዘመኑን ተማሪዎች ፍላጎት ማሟላት
v  ለትምህርት ዘመኑ የት/ቤቱን ግቢ ውብ ሳቢና ማራኪ ማድረግ
v  የት/ቤታች ግቢ አረንጓዴ በማድረግ ለህብረተሰብ በአረንጓዴ ልማት አርዓነት ያለው ተቋም እንድሆን ማድረግ














የሚከናወኑ ተግባራት
Ø  ለ2008 ዓ.ም የሚያገለግሉ ግብዓቶችን ማሟላት በዚህም ወቅት የሚሟሉ ግብዓቶች
ü  ጥቁር ሰሌዳ ፤
ü  ለ1ኛ ክፍል ራሱን የቻለ ጥቁር ሰሌዳ ፤
ü  የጽህፈት መሳሪያ
ü   የተማሪ መቀመጫ ወንበር ጥገና ማካሄድ፤
ü  የቧንቧ ጥገና ማካሄድ
ü  የት/ቤቱን አጥር ስራ መስራት
Ø  በ2007ዓ.ም ት/ቤታችን ሳቢና ማራኪ ለማድረግ ያስችል ዘንድ በግቢው የችግኝ ተከላ ማካሄድ
Ø  የ2008 ዓ.ም የተማሪዎችን መረጃ በአግባቡ ለመያዝ የሚያስችል የአመዘጋገብ ስርዓት ዘርግቶ፤
ü  መደበኛ ተማሪ፤
ü  አጸደ ህጻናት ፤ ልዩ ፍላጎት
ü  የጎልማሶች ትምህርት ተማሪዎችን ምዝገባ ማካሄድ
Ø  የት/ቤቱን አጠቃላይ ግቢና የመማርያ ክፍል ጽዳት ማካሄድና ለ2008 ዓ.ም ዝግጁ ማድረግ፡፡
Ø  የትምህርት አከፋፈት ስርዓትን የተሻለ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅትና የጽዳት ስራ ማከናወን

























በ2007ዓ.ም በክረምት ወቅት የሚከናወኑ የዝግጅት ተግባራት የድርጊት መርሃ ግብር ላልይበላ የመ/ደ/ሙ/ሳ/ት/ቤት
ተ.ቁ
የሚከናወኑ ተግባራት
ፈጻሚ
በጀት
የበጀት ምንጭ
መጠን
የሚከናወንበት ወቅት
ምርመራ
ሃምሌ
ነሃሴ
ጳጉሜ

1
የግብዓት ማሟላት ስራ መስራት
ት/ቤቱ



ü   
ü   


1.1
ጥቁር ሰሌዳ ማሰራት
ት/ቤቱ

ድጎማ በጀት
20

ü   


1.2
የጽፈት መሳሪያ ማሟላት
ት/ቤቱ
20000
መደበኛ
11

ü   


1.3
የ1ኛ ክፍል ብላክ ቦርድ መግዛት
ት/ቤቱ
21500
ድጎማ በጀት
43(ትንንሽ)

ü   


1.4
ኮምባይን ደስክ ጥገና ማካሄድ
ት/ቤቱ
10000
መደበኛ በጀት
50

ü   


1.5
የአጥር ስራ መስራት
ት/ቤቱ
6000
መደበኛ በጀት
200 ሜትር

ü   


1.6
የቧንቧ ጥገና ማካሄድ
ት/ቤቱ
3000
መደበኛ በጀት
30ና 3 አጥር

ü   


2
የችግኝ ተከላ ስራ ማከናወን
ት/ቤቱና ቀበሌው
4600
በጉልበት
1200
ü   



3
የተማሪ ምዝገባ ማካሄድ
መምህራንና ባለድርሻ አካላት


በዕቅዱ

ü   


3.1
መደበኛ ተማሪ መመዝገብ
መምህራንና ባለድርሻ አካላት


በዕቅዱ

ü   


3.2
አጸደ ህጻናትና ልዩ ፍላጎት ተማሪዎችን መመዝገብ
መምህራንና ባለድርሻ አካላት


በዕቅዱ

ü   


4
አጠቃላይ የጽዳት ስራ ማከናወን
ት/ቤቱ
500
መደበኛ
1 ጊዜ


ü   

5
የክረምትስራዎችን አፈጻጸም መገምገምና ለቀጣይ ማስተካከያ ማስቀመጥ
የት/ቤቱ አመራሮች


1ጊዜ


ü   

6
ለትምህርት አከፋፈት ዝግጅት ማድረግ
የት/ቤቱ አመራሮች
4300
ረጅ ድርጅት
1ጊዜ


ü   




No comments:

Post a Comment