አጠቃሎ (ABSTRACT)
ይህ የላልይበላ የመ/ደ/ሙ/ሳ/ት/ቤት የ2008ዓ.ም የት/ቤት ማሻሻያ እቅድ ከ2007ዓ.ም እቅድ ግምገማ በመነሳት የት/ቤታችን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ወደ ተሸለ ደረጃ ለማድረስ መሪ በመሆን ያገለግላል፡፡ ለዚህም ነው በት/ቤት ማሻሻያ መርሃ ግብር ስር የሚገኑትን 4ቱን ዶሜኖች በዝርዝር በመገምገምና እንድሁም የአጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ መርሃ ግብሮችን በማካተት እቅዱ ሊታቀድ የቻለው፡፡ በዚህም መሰረት ይህ የት/ቤት ማሻሻያ እቅድ በውስጡ፡-
Ø አጠቃላይ የት/ቤቱን ታሪካዊ አመሰራረትና አቀማመጥ
Ø የት/ቤታችን ራዕይ ተልኮ እሴቶች የአሰራር መርሆዎች
Ø የት/በታችን ምቹ ሁኔታዎችና ፈታኝ ሁኔታዎች
Ø የእቅዱ መነሻ ሁኔታዎችና የሁኔታ ትንታና
Ø የእቅድ አላማ ግብና ዝርዝር ተግባራት
Ø የእቅዱ የድርጊት መርሃ ግብር
Ø የት/ቤቱ አጠቃላይ ፊዚካል እቅድ ( የሰው ሃይልና የህብረተሰብ ተሳትፎ) በዝርዝር የያዘ ሲሆን ለእያንዳንዱ የእቅድ ተግባራት የሚከናወኑበት ስልትና በማን መቼ እንደሚከናወኑ በዝርዝር አስቀምጠናል፡፡
መግቢያ
ትምህርት ለአንድት ሃገር ሁለንተናዊ እድገት
የማይተካ ሚና አለው፡፡ ለዚህም ነው ዛሬ በአለማችን ስመ ጥር የሆኑት ያደጉና በማደግ ላይ ያሉ ሃገራት ለትምህርት ትልቅ ትኩረት
በመስጠት ሃገራቸውንና ህዝባቸውን የተሻለ ኑሮ እንድኖር ያደረጉት፡፡ኢትዮጵያም እንደ አንድ ሃገር የህዝቦቿን ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት
ከምትከተላቸው የእድገት ስልቶች መካከል አንዱና ዋነኛው ትምህርት ነው፡፡ ይህን ተግባር ለማሳካትም ሃገራችን የትምህርት ሽፋንን
በማሳደግ እረገድ ባሳለፍናቸው ተከታታይ ዓመታት አመርቂ ስራ ሰርታለች፡፡የትምህርት ሽፋን ብቻውን የአንድትን ሃገር ሁለንተናዊ እድገት
ሊያመጣ አይችልም፡፡ በመሆኑም ከትምህርት ሽፋን ጎን በጎን የትምህርትን ጥራት ለማሻሻል ይረዳ ዘንድ የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ
ፓኬጅን እንደ አንድ የሃገር ቁልፍ ተግባር በትምህርት ፖሊሲዋ ቀርጻ እየሰራች ትገኛለች፡፡ በዚህ የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ ፓኬጅም
ስድስት ተሳስረው የሚሄዱ መርሃ ግብሮችን የተነደፉ ሲሆን እነሱን ከማስተግበር አንጻርም ጥሩ የሚባል እንቅስቃሴ በሃገር ደረጃ ተስተውሏል፡፡
ሃገራዊ የትምህርት ፖሊሲን መሰረት በማድረግ
የላልይበላ መ/ደ/ሙ/ሳ/ት/ቤት ትምህርት ቤት የትምህርት ሽፋንንና የትምህርት ጥራትን እቅድ ለማሳካት በየዓመቱ ደፋ ቀና በማለት
ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም እነዚህን ታላላቅ የትምህርት ግቦች ለማሳካት ት/ቤቱ ህብረተሰቡን ያሳተፈ ስራ ማከናወን ይጠበቅበታል፡፡
ለዚህም ይረዳ ዘንድ ህብረተሰቡንና አጠቃላይ የትምህርት ባለ ድርሻ አካላትን በንቃት ሊያሳትፍና ውጤት ሊያመጣ የሚችል የ2008ዓ.ም
የት/ቤታች የህዝብ ንቅሳቄ እቅድ አቅደናል፡፡
መነሻ
ሁኔታ
የአገራችን የትምህርት ሥርአት በአቅርቦቱ፣ በፍትሐዊነቱ እና
በሽፋኑ ረገድ መሠረታዊና እመርታዊ ለውጦች የታዩበት ቢሆንም በጥራቱ ረገድ ችግሮች ያሉበት መሆኑ በመረጋገጡ የአጠቃላይ ትምህርት
ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ ተቀርጾ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ ፓኬጁን በተሟላ ሁኔታ ለመፈፈጸም የሚቻለው ፈፃሚውን አመራሩን፣ባለድርሻ አካሉንና
መላውን ህዝብ በፓከጁ ዙሪያ በማሰባብና በጋራ በማነቃነቅ መሆኑ ግንዝቤ ተወስዶ ባለፉት አመታት የንቅናቄ ዕቅድ ተዘጋጅቶ በተደረገው
ርብርብ አበረታች ውጤቶች ባይመዘገቡም የተወሰነ ለውጥ እንዳለ የሚያመላት ነገር አለ፡፡ የ2007 ዓ.ም. የንቅናቄ እቅድ ዋና አላማ
በት/ቤታችን የትምህርት ልማት ሠራዊት በመገንባት ሁሉም መምህራንና የትምህርት ባለ ድርሻ አካላት ፓኬጁን አቀናጅቶ በመፈፀም የትምህርት
ጥራትን ማረጋገጥ ነበር፡፡
ከዚህ አኳያ የ2007 ዓ.ም. የንቅናቄ እቅድ አፈጻጸምን ስንመለከት ተወሰኑ ጅምር ተግባረቶች ማከናወን ቢቻልም እንኳ ከሚጠበቀው ውጤት
አንጻር ስንመለከተው ራሱን የቻለ ጉድለት ነበረበት፡፡ ለዚህም ዋና ምክንያቱ በት/ቤት ያለው አመራር የትምህርት ልማት ሠራዊት ማደራጀት ቢችልም በአንድ ዓይነት
አስተሳሰብ ወደ ሥራ አለማስገባት፣ የአመለካከትና የክህሎት ችግሮቹን
ለይቶና አስተካክሎ የመሪነት ሚና አለመጫወት፣ የምዕተ አመቱን ግብ ለማሳካት እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሕጻናትን ወደ ት/ቤት
እንዲገቡ የራስን ድርሻ አለመወጣት፣ በየደረጃው ትምህርት አመራሩና በመምህራን ዘንድ የሚታዩ የአመለካከት ችግሮችን ለይቶ በትግል
ያለማስተካከል፣ እስከ ክፍል ወርዶ ለውጥ የሚያመጣ ድጋፍ አለመደገፍ፣ የት/ቤት ልዩ ልዩ አደረጃጀቶችን እንዲጠናከሩ በየወሩ ለውጥ
የሚያመጡ ልዩ ልዩ ተግባራትን ቀርጾ አለመስጠትና መተግበራቸውን አለመከታተል ካተተገበሩም ለቀጣይ ምን መሰራት እንዳለበት ከመምህራን
ጋር ተከታታይና ለውጥ የሚያመጣ ድጋፍ አለማድረግ የሚሉት በግምገማው
የተለዩ ዋና ዋና ችግሮች ነበሩ።
ከላይ ካነሳነው ሃሳብ በተጨማሪም የትምህርት አመራሩ የተሻለ መነሳሳት የፈጠረ ቢሆንም ቀጣይነት ባለው መልኩ ድጋፍ የመስጠት፣
የማነሳሳትና እየታገለ ወደ ተሟላ የትምህርት እንቅስቃሴ ውስጥ አለመግባቱ፣የትምህርት ልማት ሠራዊት ከማደራጀትና ከመምራት አኳያ የተሟላ የሥራ ክፍፍል አድርጐ በትምህርት ባለድርሻ አካላቶች መካከል ተመጋጋቢ በሆነ መስተጋብር ንቅናቄ ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ ሚናውን እየተወጣ አለመሆኑ፣ እና መሰል የትምህርት ስራውን
ውጤታማ ያላደረጉ ተግባራቶች መኖራቸው ታውቋል፡፡
በአጠቃላይ የ2007 ዓ.ም. የንቅናቄ እቅድ አፈጻጸም ሲታይ ፓኬጁን በተደራጀ የትምህርት ልማት ሠራዊት በመፈፀም የትምህርት
ጥራትን ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶች ያዝ ለቀቅ የሚታይባቸውና ተከታታይነት ባለው መልኩ የተጠናከረ
የክትትልና ድጋፍ ግብረ መልስ ሥርዓት በመዘርጋት የሚፈፀሙ ባለመሆናቸው በቀጣይ የተጠናከረ ሥራ መሥራትን ይጠይቃል፡፡ ስለዚህ በ2008
ዓ.ም. በየደረጃው የሚታዩ ችግሮችን በትምህርት
ቤት የትምህርት ልማት ሠራዊት በመገንባት፣ በማደራጀትና ወደ ሥራ በማሠማራት እንዲሁም ምርጥ ተሞክሮዎች በመቀመርና በማስፋት ፓኬጁን
በተቀናጀ መልኩ በሁሉም መምህራንና የትምህርት ባለ ድርሻ አካላት መተግበር ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም ሥራ መላ ህብረተሰቡን በተለይም
ግንባር ቀደሙን ኃይል በማነቃነቅ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የት/ቤቱን ብሎም የወረዳውን የትምህርት ስራ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር
ይረዳ ዘንድ ይህ የህዝብ ንቅናቄ ዕቅድ ተዘጋጅቷል።
የዕቅዱ አስፈላጊነት
የአጠቃላይ ትምህርት ለህፃናት የወደፊት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና
ፖለቲካዊ ህይወት መሰረት የሚጣልበት ወሳኝ ደረጃ ነው፡፡ ከዚህም
አኳያ ሀገራችን የነደፈችውን ፖሊሲና ስትራቴጂዎች እንዲሁም የ2ኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ተግባራዊ ሊያደርግ የሚችል
ብቁ ዜጋ ለማፍራት መሠረት ይጥላል። የምንሠጠው ትምህርት በየደረጃው የሚያስፈልገውን የሰለጠነ የሰው ሃይል በማፍራት ከግብርና መር
ወደ ኢንዱስትሪ የሚደረገውን ሽግግር ውጤታማ የሚያደርግ ብቁ ዜጋ መፍጠር ካልተቻለ የተጀመረውን የኢኮኖሚ እድገት ማስቀጠል ሳይሆን
ወደኋላ መመለስ ሊከሰት ይችላል። ስለሆነም በትምህርቱ ዘርፍ እየሠራን
ያለውን ሥራ ቆም ብለን በማየትና በመፈተሽ ሀገራችንን በአጭር ጊዜ ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ለማሰለፍና
ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ የመዋቅር ሽግግር ለማምጣት መሠረት እየጣልን መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።ይህንን ማድረግ የሚቻለው ደግሞ
በየደረጃው የሚሰጠው ትምህርት ጥራቱ የተጠበቀ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
ከዚህ አንፃር የት/ቤታችን የትምህርት ስራ ውጤት ስንመለከት የጥራት ችግሮች ያሉበት መሆኑን መረዳት ቀላል
ነው፡፡ለአብነትም፡- በተለያዩ ጊዜያት በት/ቤቱ የተካሄዱ የኦድት ፈተና ምዘና ውጤቶችና አጠቃላይ የት/ቤቱ የ2007ዓ.ም ውጤት
የሚያሳዩት በየክፍል ደረጃው ያለው የተማሪዎች ውጤት በሚፈለገው ደረጃ እየተሻሻለ ባለመሆኑ በትምህርት ጥራት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥተን
መስራት ያለብን መሆኑን ነው።
የላልይበላ የመ/ደ/ሙ/ሳ//ቤት ሃገራችን የጣለችውን የትምህርት
ስራ ግብ ለማሳካት የተቻለውን ሁሉ ለማድረግ ደፋ ቀና ሲል ዓመታትን አሳልፏል፡፡ ነገር ግን ህብረተሰብን ማዕከል ያላደረገና ህብረተሰብን
ያላሳተፈ የትምህርት ስራ ውጤታማ እንደማይሆን በማወቅ ይህን የህዝብ ንቅናቄ እቅድ አቅዷል፡፡ ስለዚህ የህዝብ ንቅናቄ እቅዱ ህብረተሰቡንና
የትምህርት ባለድርሻ አካላትን ወደ ትምህርት ስራው በማስገባት የትምህርት ጥራት እንድጠበቅ ለማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ስለሆነም
የት/ቤቱን የትምህርት ልማት ሠራዊት በማደራጀትና በማንቀሳቀስ መላ ህብረተሰቡን እንዲያነቃነቅ በማድረግና በትምህርት ስራ በወኔ
እንድዘምት በማድረግ የትምህርትን ጥራት ለማረጋገጥ እንዲቻል ይህን እቅድ ማዘጋጀት አስፈልጓል፡፡
ዓላማ
v
በት/ቤታችን
የትምህርት ልማት ሠራዊት በማደራጀትና በመምራት ግንባር ቀደሙን ሀይልና መላ ህብረተሰቡን አቀናጅቶ በማነቃነቅ የተጀመረውን የትምህርት
ተሳትፎ ስራን አጠናክሮ በማስቀጠል የትምህርት ጥራት ላይ መሠረታዊ
ለውጥ ማምጣት ነው።
v
የዚህ
ዕቅድ ዋነኛ ዓላማ የት/ቤታችን የትምህርት ጥራት በማስጠበቅ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሁኔታው የሚፈልገውን የሰው ኃይል
በማፍራት ሀገሪቱን ከድህነት ለማላቀቅ የሚደረገውን ጥረት ማገዝ ፡፡
v በት/ቤት
ጠንካራ አመራር በመፍጠር ወላጆችና መላው ህብረተሰብ ለት/ቤት መሻሻል ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ በማድረግ፣ ምቹ የትምህርት ቤት አካባቢ
መፍጠርና የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል፡፡
v ለትምህርት
አስፈላጊ የሆኑ ግባአቶችን በሟሟላት በየደረጃው የተቀረፁ ሥርዓተ ትምህርቶችን ለመተግበር የሚያስችሉ ሁኔታዎችን በማመቻቸት የትምህርትን
ጥራት ማሻሻል፣
v በመልካም
የዜግነት እሴቶች የታነጸ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሃላፊነትን በብቃት መወጣት የሚችል ዴሞክራሲያዊ ባህሉ የዳበረ ብቁ ዜጋ
ማፍራት፣
ዕቅዱን ለማስፈፀም የምንከተላቸው አቅጣጫዎች
ይህንን
አላማ ለማሳካት የምንከተላቸው አቅጣጫዎች ፦
በት/ቤታችን
የሚከናወኑ ተግባራትን በህብረተሰብ ተሳትፎ አጅቦ መስራት፣
በት/ቤቱ
የሚገኘውን ግንባር ቀደም ሀይል አቅም በመገንባት በተደራጀ መልኩ እንዲንቀሳቀስ ባለፈው አመት የጀመርነውን መልካም ስራ አጠናክረን
መቀጠል፣
የት/ቤትና
ቀበሌ አመራሩ ፓኬጁን ተገንዝቦ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል እያደረገ የጀመረውን አመራር አጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግ፣
በፖሊሲና
ስትራቴጂ ጉዳዮች እንዲሁም በፓኬጁ አፈጻጸም ሂደት የሚታዩ የግንዛቤና የአመለካከት ክፍተቶችን በመለየት አባላት በህዋሳት፣ በልማት
ቡድኖችና በየደረጃው ባሉ የ1ለ5 አደረጃጀትና ኮሚቴዎች እየተወያዩ ግንዛቤያቸውን የሚያዳብሩበትና ተገቢውን መረጃ በወቅቱ እያገኙ
አቅማቸውን የሚያጐለብቱበትን አሰራር አጠናክሮ መቀጠል፣
በመምህራንና በወላጆች እንድሁም በትምህርት አጋር አካላት ላይ ያሉ የግንዛቤና
የክህሎት ክፍተቶችን ለመሙላት ተከታታይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስራ መስራት፣
በት/ቤት
ደረጃ የሚገኙ የተለያዩ አደረጃጀትን የሚመሩ አመራሮች ድጋፍ እንዲያገኝ ማድረግና እንዲሁም ከዘመቻ ሥራ ወጥቶ በዘላቂነት ወጥ የሆነ
ሥራ እንዲሠራ ማድረግ፣
በትምህርት
ቤታች የተቋቋሙትን አደረጃጀቶች በስፋት በመጠቀም የተጀመረውን የለውጥ
ስራ አጠናክሮ መቀጠል፡፡
ስኬታማ
ተግባራትን ያከናወኑ አደረጃጀቶችና የአደረጃጀት መሪዎች የሚበረታቱበት እንዲሁም ሃላፊነታቸውን የማይወጡትም የሚጠየቁበት ሥርአት
መዘርጋትና ተግባራዊ ማድረግ፡፡
የትምህርት
ባለድርሻ አካላትን በበቂ ሁኔታ አደራጅቶ ማሳተፍና የየድርሻቸውን እንዲወጡ ማስቻል፣
በት/ቤታችን
የሚገኘውን ሰብአዊና ቁሳዊ እንዲሁም የገንዘብ አቅም በተገቢው መጠቀም፣
በፓኬጁ
የሚከናወኑ ተግባራት መቼና በማን ሊፈጸሙ እንደሚገባቸው በመለየት ማከናወንና
አፈፃፀሙን በቼክሊስት መሰረት የመገምገም፣ የመደገፍና ግብረ መልስ የመስጠት ሥርአት መዘርጋት አጠናክሮ መቀጠል የፈጻሚዎችን
ደረጃ መለየት
ምርጥ ተሞክሮ መቀመርና
መጠቀም
የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጁን በብቃት
ለመፈፀም እንዲቻል አንዱ ስልት በፓኬጁ አተገባበር ሂደት ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመርና በማስፋት ስትራቴጂው መሠረት መተግበር ነው፡፡
በዚህም መሠረት በአገሪቱ
በአንድ አካባቢ ተሞክረው ውጤታማ የሆኑ አሰራሮችን በየደረጃው በመለየት እንዲሁም ተቀምረው ወደ ሌሎች ትምህርት ቤቶች ማስፋት የሚኖረውን
ፋይዳ በመገንዘብ መንቀሳቀሳችን መጀመራችን ይታወቃል። በተለይም ባሳለፍነው
በ2007ዓ.ም ከ5 በላይ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመለየት ለሌሎች እንድሰፉ ከማድረግ አንጻር አበረታች ስራ ተከናውኗል፡፡ ይህ ተግባር
ከባለድርሻ አካላት ጋር አብሮ በመስራት በሁሉም ትምህርት ቤቶች ዘላቂነት ያለው አዎንታዊ ለውጥ በአጭር ጊዜ በማምጣትና የፓኬጁን
መተግበር በማሳለጥ ተማሪዎች ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኙ ለማድረግ የሚያስችል አሰራር ነው፡፡
በዚህ መሠረተ ሃሳብ መነሻነት በየደረጃው ምርጥ
ተሞክሮ የመቀመርና የማስፋፋት ሥራ የተጀመረ ቢሆንም በሂደቱ በርካታ ችግሮች ተስተውለዋል። ዋና ዋናዎቹን ለመዘርዘር
ያህል፣
- ከሌሎች ለመማር ዝግጁ አለመሆን፣ ማጥላላት፣ ተሞክሮን ቀምሮ በማስፋት
ሊገኝ የሚችለውን ፋይዳ ጠንቅቆ አለመገንዘብ፣ ሌላ ሰው ቀምሮ እንዲሰጠው መጠበቅ፣ ተሞክሮዎች ከራስ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አዛምዶ
አለመተግባር፣
- ተሞክሮዎችን
የመለየትና የመቀመር ክህሎት ማነስ፣ አመራሩም ትኩረት ሰጥቶ በእቅድ እንዲያዝ አለማድረጉ፣
- በየደረጃው
ተሞክሮዎችን ለይቶ በመቀመር ለማስፋት የተጣለውን ግብ ችላ ማለትና ከላይ ብቻ በመጠበቅ የራስን ድርሻ አለመወጣት፣
- መልካም
ተሞክሮ ከሩቅ ቦታ ብቻ እንደሚገኝ አድርጎ ማሰብና በአቅራቢያ ያሉ ተሞክሮዎችን ትኩረት ሰጥቶ አለመንቀሳቀስ፣
- ተቀምረው የቀረቡ ተሞክሮዎችን ፈጻሚውን ሀይል አወያይቶና
አብቅቶ ከመተግበር ይልቅ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በመለጠፍ ወይም በደብዳቤ ለትምህርት ክፍሎች በማስተላለፍ ለማስፈጸም መሞከር፣
- የተቀመሩ
ተሞክሮዎችን ለባለድርሻ አካላት አስተዋውቆና በቂ ግንዛቤ አስይዞ ወደ ተግባር አለመግባት፣ ተግባራዊ እየሆኑ ያሉትንም በዘላቂነት
በሁሉም ክፍሎችና መምህራን ለማስቀጠል የሚያስችሉ ሥራዎችን አለመሥራት፣
- ተሞክሮዎችን በተወሰኑ
በተወሰኑ መምህራን ብቻ ማሰራት እንደ መጨረሻ ግብ አድርጐ መውሰድ፣እና የመሳሰሉትን ችግሮችን መጥቀስ የሚቻል ሲሆን በቀጣዩ በ2008 ዓም የትምህርት
ዘመን እነዚህን ችግሮች አስወግደን በየደረጃው ተሞክሮን ከመለየት ፣ ከመቀመርና ከማስፋት አኳያ የሚታዩ የአመለካከት፣ የክህሎት፣
የግብአት አቅርቦት፣ የክትትልና ድጋፍ ችግሮችን ለማስወገድ የሚያስችሉ አሰራሮች ትኩረት እንዲያገኙ በማድረግ ቢያንስ በወጥነት
ሊያሠራ የሚያስችል ስልትና እቅድ ነድፎ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡
2.1
ዓላማ
የተደራጀ የት/ት የልማት ሰራዊት በመገንባት ብልሹ አመለካከትንና ተግባርን ታግሎ በማሸነፍና የትም/ት ዘርፍ እቅዶችን
በውጤታማነት በማስፈፀም የትምህርት ተሳትፎን ማሳደግና የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ፡፡
2.2
ግቦች
1.
በአመለካከት በአሰራርና በአደረጃጀት የተስተካለ
ቁመና ያለው የትምህርት ስራ ፈፃሚ(መምህር)ና ባለድርሻ አካላት በመፍጠር የተደራጀ የትም/ት የልማት ሰራዊት መገንባት
2.
በትምህርት ቤታችን የሚሰጠውን አጠቃላይ ትምህርት ጥራቱን የጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ
3.
በቀበሌያችን የትምህርት ፍትሃዊነት ተደራሽነት
ማረጋገጥ ማለትም ፡-
*
በ2008 ዓ.ም ዕድሜአቸው ለትምህርት የደረሱና
ነባር ተማሪዎችን ሙሉ በሙሉ እንዲገቡ በማድረግ ጥቅል ተሳትፎን 100 % ማድረስ፡፡
*
የቅድመ መደበኛ ትምህርትን ሽፋን 50% ማድረስ፡፡
*
የተቀናጀ ተግባር ተኮር ትምህርት በቀበሌው
ውስጥ በማስፋፋት ከ500 በላይ ማንበብ መፃፍ የማይችሉትን ጎልማሶችን በማስተማር ከህይወት ክህሎት ጋር አቀናጅቶ ማንበብ መፃፍ
የሚችሉ ጎልማሶች ማድረግ፡፡
4.
የት/ቤቶችን የመሰረተ ልማት እና የግብአት
ችግሮችን በመፍታት ት/ቤቱ ለመማር ማስተማሩ ስራ ምቹ ማድረግ፡፡
5.
የትምህርት ስርዓቱን ከአደናቃፊ አመለካከትና
ተግባራት ማፅዳት፡፡
2.3 ግቦቹን ለማሳካት መከናወን ያለባቸው ቁልፍ አብያተ ተግባራት
v በአመለካት በአሰራርና በአደረጃጀት የተስተካከለ ቁመና ያለው የትምህርት ልማት ሰራዊት መገንባት
2. አብይት ተግባራት
ሀ. በት/ቤታችን የሚሰጠውን የትምህርት ጥራት ማስጠበቅ
ለ. የትምህርትን ፍትሃዊነትና ተደራሽነት ማሳደግ
·
የመደበኛ ትምህርትን አጠናክሮ በመቀጠል መጠነ
ማቋረጥን ከ1 ፐርሰንት በታች ማድረስ
·
የቅድመ መደበኛ ትምህርትን በማጠናከር በቀበሌው
የሚገኙ እድሚያቸው ከ4-6ዓመት የሆኑ ህጻናትን የዕድሉ ተጠቃሚ ማድረግ
·
የተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርትን ማስፋፋትና
አጠናክሮ ማስቀጠል
ሐ.
የት/ቤቱን የመሰረት ልማት እና ግብአት ችግሮችን በመፍታት ት/ቤቱ ለመማር ማስተማሩ ስራ ምቹ እንዲሆን ማድረግ
መ. የትምህርት ስርዓቱን አደናቃፊ አመለካከቶችና ተግባራት ማፅዳት
2.4
የቁልፍና ያብያት ተግባራት ዝርዝር አፈፃፀም
1. በቅድመ ዝግጅት የሚከናወኑ ተግባራት
1.1
የቀበሌ
አመራርን ፤ፈፃሚዎችን መምህራንና የትምህርት ባለድርሻ አካላትን አቅም መገንባት
ሀ. የቀበሌ አመራሩንና የት/ቤት አመራሩን የተደራጀ የልማት ሰራዊት መሪ እንዲሆን ማስቻል በ2007 ዓ፣ም ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አስመልክቶ የሂስና ግለሂስ የደረጃ ምደባ በማካሄድ ያለባቸውን
ክፍተቶች ለመሙላትና እንዲገነዘቡ በማድረግ አቅሙን እንዲገነባ ማድረግ፡፡


ለ. የመምህራንን የመፈፀም አቅም በመገንባት የተደራጀ የትምህርት
ልማት
ሰራዊት ቁመና ላይ ማድረስ


*
ለመምህራን ወደ ተማሪው ውጤት መሻሻል የሚያተኩር
ውጤት ተኮር ቀርፆ መስጠትና ተግባራዊነቱን በየወቅቱ መከታተል
*
በአሰራር ሂደቱ ላይ ግንዛቤና የክህሎት ክፍተቱን
በሚሞላ መልኩ ግንዛቤ መፍጠር
*
መምህራን የሚያነሷቸው ጥያቄቆችና ችግሮች
ወይም እንቅፋቶች ካሉ መፍትሔ ማስቀመጥ
ሐ. የህዝብ አደረጃጀቶችን በመገንባት የተደራጀና የትምህርት ልማት ሰራዊት አባል ሁነው እንድቀጥሉ
ማድረግ
*
የቀበሌ ትምህርት ስልጠና ቦርድና ወ.መ.ህ.ን
አፈፃፀማቸውን ለመገንባት በአዲስ መልክ ማደራጀት ሃላፊነታቸውንና ተግባራታቸውን ማሳወቅ
*
በእቅዱ ላይ የብሎክ፤ የሴት ልማት ቡድን ፤የወጣቶች አደረጃጀት አመራሮችን ግንዘቤ መፍጠር
*
ለህብረተሰቡ ለመምህራን ለወ.መ.ህ.ና ቀ.ት.ስ.ቦ. ለተማሪዎች የእቅድ ማስተዋወቅ ስራ
በመስራት በሁሉም ዘንድ ተነሳሽነት መፍጠርና የትምህርት ስራው ዋና አጋዥ አድርጎ ማደራጀት
መ. የድርጅት አባሉን አቅም በመገንባት የተደራጀ የትምህርት የልማት ሰራዊትመፍጠር
*
ለድርጅት አባሉ የእቅድን ኦሬንቴሽን መስጠት
*
የአባላትን የመፈፀም አቅም በመገንባት ተልእኮዎችን
ቆጥሮ መስጠት፤ መቀበል ግብረመልስና ደረጃ ማውጣት
*
የተማሪዎች ህዋስን በማጠናከር የተማሪዎችን
ሁለንተናዊ ለውጥ በራሳቸው እየገመገሙ እንድመሩ ማስቻል፡፡
*
የአባላቱን የጠራ መረጃ መያዝና ለሚመለከተው
አካል ስንጠየቅ በወቅቱ ጥርት ያለ መረጃ መስጠት
1.2.
አሰራርና አደረጃጀት ችግሮችን ማስተካከል
v መ/ራንን በልማት ቡድን በ1፡5 በወመህ በቀ.ት.ቦ፤
በህዋስ ፤በድፓርትመንት፣በኮሚቴ ና ክበባት እንድሁም ልዩ ልዩ ፎረሞች ማደራጀት
v በክፍል ደረጃ
የክፍል ወተመህን በማደራጀት ስራ በመስጠት በመቀበል በመገምገም የየክፍሉን የመማር ማስተማር ስራና የተማሪዎችን ስነ ምግባር እየገመገሙ
እንድመሩ ማድረግ
v ተማሪዎችን በክበባትና ኮሚቴዎች በህዋሳት
በትምህርት ልማት ቡድን በክፍል ውስጥ በ1፡5 አደረጃጀት፤ በአለቆች
ህብረት፤ የጎበዝ ተማሪዎች ህብረት፤ የተማሪዎች ፓርላማ በማደራጀት ራሳቸውን በራሳቸው በማስተዳደረ የዴሞክራሲ ስርዓትን የማስለመድ
እንድሁም ያላቸውን ተሰጥኦ የሚያወጡበት ስርዓት መዘርጋት፡፡
-የቀበሌ አደረጃጀቶችን ማጠናከርና ለትምህርት ስራው ደጋፊ እንድሆኑ ማድረግ
1.3
ግብአትን ማሟላት
ü የተሰባበሩ የውሃ ቦኖችን በማስጠገን ተማሪዎችና የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ
ü የተበዳደሱ ሰሌዳዎችንና ወንበሮችን ሙሉ በሙሉ
መቀየር
ü 35 ኮንፓይንድ ዴስኮችን ማሰራት ሌላ 50 ወንበር ማስጠገንና የተማሪዎችን መቀመጫ በስታንዳርዱ መሰረት
ማድረስ
ü ያረጁ መማርያ ክፍሎችን ሙሉ በሙሉ የመጠገን
ስራ መስራት፡
ü ልዩ ልዩ የጽህፈት መሳሪያዎችን ቢያንስ በዓመት
2 ጊዜ ግዥ እንድፈጸም በማድረግ ለትምህርት ስራው የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ቀድሞ ማሟላት፡፡
ü ለቤተ ሙከራና ቅርንጫፍ ማዕከል ልዩ ትኩረት
በመስጠት ለተማሪዎች መማርያ የሚያገለግሉ ግብዓቶችን ማሟላት፡፡
1.4
የዝግጅት ምዕራፍ ትግበራትን በጥራት ለመፈፀም የክትትልና ድጋፍ ስርዓት ዘርግቶ ተግባራዊማድረግ
በተደራጀው የልማት ሰራዊት ቡድን ስራውን
ዘወትር ረቡዕ መገምገም በዕለቱ በሪፖርት እንድያሳውቁ ማድረግ
በተገመገመው ውጤት መሰረት ችግር ያለበትን
መለየት ከመምህራን ጋር በግብረ መልስ መወያየትና ድጋፍ መስጠት
2 በትግበራ ምዕራፍ የሚከናወኑ ተግባራት
2.1 የ2008 አመትን ንቅናቄ መጀመር
Ø የትምምህርት ሳምንት በደመቀ ሁኔታ በማክበር የአመቱን ትምህርት በተነሳሽነት መጀመር
Ø ነባር ተማሪዎች በሙሉ ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ማድረግ
Ø እድሜአቸው ለትም/ት የደረሱ ህፃናት ሁሉም ትምህርት ቤት እንዲገቡ ማድረግ
Ø እድሜአቸው ከ4-6 ዓመት የሆናቸውን ህፃናት ወደ ቅድመ መደበኛ ማስገባት
Ø መምህራንና ህብረተሰቡ በትምህርት ቤቱ ችግሮች ዙሪያ በማዎያየት ንቅናቄ ውስጥ ማስገባት
Ø በክረምት እቅድ አፈጻጸም ላይ ጥሩ አፈጻጸም ላሳዩ ባለድርሻ አካላት የማበረታቻ ስርዓት በመዘርጋት
ለቀጥይ የትምህርት ስራ ዝግጁ እንድሆኑ ማድረግ፡፡
2.2 በተደራጀ የት/ት የልማት ሰራዊት አማካኝነት የት/ት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጁን
በውጤታማነት መፈፀም፡፡









3. በተደራጀ የትም/ት የልማት ሰራዊት አማካኝነት የት/ት ተሳትፎን
ማሳደግ
*
የቅድመ መደበኛ ትምህርት ተሳትፎን 50%
ማድረስ
*
ንጥር ቀበላን 100% ጥቅል ተሳትፎን
100% ማድረስ
*
የማቋረጥ መጠንን ከ1% በታች ዝቅ ማድረግ
*
ጎልማሶችን በበ4 ጣቢያዎች ጣቢያዎች እንዲማሩ
ማድረግ
3. የትግበራ ምዕራፍ ትግበራትን በጥራት ለመፈፀም የለውጥ አመራርን በብቃት መወጣት
ሀ. በተግባር ወቅት የሚከሰቱ አፍራሽና አደናቀፊ አዝማሚያውን መለየት ማጋለጥና መተጋል ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ
እንድመጡ ማድረግ
*
የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባራትን ከነምንጫቸው በጥናት መለየት፤መታገልና ማድረቅ
*
በት/ቤቱ ውስጥ የሚታዩትን የትም/ት ስርዓቱን ከፍተኛ አደጋ ላይ የሚጥሉ የተበላሹ ልምዶችን ለመታገል የሚያስችሉ
ልዩ ልዩ ስልቶችን መጠቀም
ለ. ምርጥ ተሞክሮን እየቀመሩ ትምህርት መውሰድና በሁሉም ትምህርት ክፍሎች ማስፋት ተግባራዊ ማድረግ
ሐ. በተግባር ሂደት የሚከሰቱ የክህሎት ክፍተቶችን እየለዩ በልዩ ልዩ ስልጠናዎች መሙላት
መ. አደረጃጀቶችን በማጠናከርና
አሰራሮችን በተግባር መሳሪያነት መጠቀም
*
የመ/ራን የልማት ሰራዊት የተማሪዎች የ1፡5 አደራጃጀት የብሎክ አደረጃጀት ክበባት፣ትም/ት ክፍሎችን በቁልፍና
በአብያት ተግባራት ለተገለፀው ተግባራት ማስፈፀሚያነት መጠቀም፡፡
*
ሁሉም አደረጃጀቶች እቅድ እንዲኖራቸውና በእቅድ እንዲመሩ ማድረግ አፈፃፀማቸውን መገምገምና ግብረ መልስ መስጠትና ማስተካከል፡፡
ሠ. የቀረበን ግብአትና ቴክኖሎጂ በብቃት መጠቀም
*
የተማሪ መፅሀፍትን በጥንቃቄ ለተማሪው እንዲደርስ
ማድረግና በአግባቡ እንድይዙ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ መስራት
*
የቤተ-ሙከራ ፣የቤተ-መፅሀፍ እና ቅርንጫፍ
ማዕከል ተሟልተው ለተማሪው አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ
*
የቅርንጫፍ ማዕከል በተገቢው መንገድ መረጃ
መሳሪያ የማምረት ና የሚጠቀሙበት እንዲሆን ማስቻል
*
የሬዲዮ ትምህርት በአግባቡ ተግባራዊ ማድረግ
*
የሚኒሚዲያ አገልግሎት በጥራት መጠቀምና የት/ቤቱን
ስራ ማስተዋወቅና ለተማሪዎች መረጃ እንድደርስ ማድረግ
*
ለመምህራንና ለተማሪዎች የኮምፒውተር ስልጠና
እንድያገኙና የኢንተርኔት ተጠቃሚ እንድሆኑ ማድረግ
4. የትግበራ ምዕራፍ ተግባራትን በጥራት ለመፀም የሚያስችል በድጋፍና
ክትትል ሥርዓት ዘወትር ተግባራዊ ማድረግ
*
በተደራጀው የትምህርት የልማት ሰራዊት ዘወትር
እሮብ በመገኘት ያለውን ሁኔታ መከታተል ችግሩን መለየት መደገፍና ማስተካከል፡፡
*
የመምህራን ደረጃ ተቆጥሮ በተሰጠው ስራ መሰረት
በየሳምንቱና በየወሩ መገምግም ደረጃ ማውጣት ማበረታታት
3 የማጠቃለያ ምዕራፍ
*
የ2007 ዓ.ም የአጠቃላይ የስራ ግምገማ
በማካሄድ መልካም ትምህርቶችንና መሻሸል የሚገባቸውን እንዲሁም ተሞክሮዎችን መለየት
*
ከግባቸው የደረሱ ትምህርት ክፍሎችን ፤መምህራንን፤
ተማሪውን፤ መለየት የገንዘብ የመፀሀፍት የምስክር ወረቀት መሸለም
*
ሂስና ግለሂስ ከግምገማው በመነሳት ማካሄድና
ለአደረጃጀት መሪዎች ለመምህራን ደረጃና ምደባ መስጠት
*
አፈፃፀማችን የደከሙ ተግባራቶች ዝርዝር መረጃ
መያዝና ለቀጣይ የዕቅድ ዝግጅት ግብአት መያዝ
*
ዝቅተኛ አፈፃፀም ላላቸው የንቁ ደወል ጥሪ
የምስክር ወረቀት መስጠት፡፡
4 የአፈፃፀም አቅጣጫዎች
·
በት/ቤት የተደራጀው የልማት ሰራዊት ቡድን
በየሳምንቱ እሮብ ስራውን እየተገመገመ የመምራት አቅጣጫን ይከተላል
·
ስራ በየሳምንቱ እየተቆጠረ ለመ/ራን ይሰጣል
ደረጃ ይወጣል ግብረ መልስ ይሰጣል፡፡
·
የተማሪና የመምህር ህዋሳትና በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እየተገናኙ በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይትና
ግምገማ በማካሄድ ግንባር ቀደም የሆኑትና ሃላፊነታቸውን እየተወጡት መሆናቸውን ማረጋገጥ፡፡
·
ህብረተሰቡ እና የተማሪ ወላጆች በየወሩ በክፍል ደረጃ ስራቸውን እንዲገመገሙ ማድረግ አቅጣጫን እንከታተላለን፡፡
·
እያንዳንዱ ተግባራት ለተቀመጡለት የጊዜ ሰሌዳ
መሰረት እየፈፀመ መሆኑን የመከታተልና በግብረ መልስ የማሳወቅ አቅጣጫ፡፡
·
የስራ ግምገማ በየወሩ በመምህራን ጉባኤ ማካሄድና
ጠንካራና ደካማ ጎንን የማስቀጠል አቅጣጫ፡፡
·
ምርጥ ተሞክሮውን በመቀመር የማስፋፋት አቅጣጫን
መከተል፡፡
የላልይበላ የመ/ደ/ ሙ/ሳ/ት/ቤት የ2008
ዓ.ም የህዝብ ንቅናቄ መፍጠሪያ እቅድ የድርጊት መርሀ-ግብር
ተ.ቁ
|
የሚከናወኑ ተግባራት
|
መለኪያ
|
መጠን
|
የበጀት ምንጪ
|
በጀት
|
የክንውን ወቅት
|
||||||||||||
ብ
|
ሣ
|
1ኛ ሩብ ዓመት
|
2ኛ ሩብ ዓመት
|
3ኛ ሩብ ዓመት
|
4ኛ ሩብ ዓመት
|
|||||||||||||
ሀ
|
ነ
|
መ
|
ጥ
|
ህ
|
ታ
|
ጥ
|
የ
|
መ
|
ሚ
|
ግ
|
ሰ
|
|||||||
1
|
በ2007 ዓ፣ም ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አስመልክቶ የሂስና ግለሂስ የደረጃ ምደባ በማካሄድ ያለባቸውን
ክፍተቶች ለመሙላትና እንዲገነዘቡ ለማድረግ አቅሙን እንዲገነባ ማድረግ
|
በቁጥር
|
1
|
-
|
-
|
-
|
1
|
|||||||||||
2
|
የ2007 ዓ.ም የእቅድ ዝግጅት ኦሬንቴሽን ላይ ተመስርቶ መ/ራንን በብቃት ማዘጋጀት የአቅም ግንባታ
ማካሄድ የአመለካከትና የእቅድ የማቅድ የክህሎት ችግሮችን በሚፈታ መልኩ መ/ራንን የማዘጋጀት ስራ ይሰራል፡፡
|
በቁጥር
|
1
|
-
|
-
|
-
|
1
|
|||||||||||
3
|
በ2007 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ላይ ተመስርቶ በተለይም ቁልፍ ተግባር አፈፃፀም ሂደት
የነበሩ የግንዛቤ ችግሮች የክህሎት እጥረቶች የአሰራር (የውጤትተኮር) የስራ ስነ-ምግባር እንዲሁም የአደረጃጀት (የልማት ቡድኖች
የ1፡5) ክፍተቶችን ማሻሻያ ላይ የአፈፃፀም ግምገማ ሂስና ግለሂስ
እንዲሁም የደረጃ ምደባ በማድረግ ለቀጣይ ስራ መነሳሳት መፍጠር
|
በቁጥር
|
1
|
-
|
-
|
-
|
1
|
|||||||||||
4
|
በ2008 ዓ.ም እቅድ ተነስቶ መ/ራንን በብቃት ማዘጋጀት
·
ለመ/ራን ውጤት ተኮር ቀርፆ መስጠት
·
በአሰራር ሂደቱ ላይ ግንዛቤና የክህሎት
ክፍተቱን በሚሞላ መልኩ ግንዛቤ መፍጠር
·
መ/ራን በሚያስቀምጣቸው ችግሮች መፍትሔ
ማስቀመጥ
|
በቁጥር
|
10
|
-
|
-
|
-
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
||
ተ.ቁ
|
የሚከናወኑ ተግባራት
|
መለኪያ
|
መጠን
|
የበጀት ምንጪ
|
በጀት
|
የክንውን ወቅት
|
||||||||||||
ብ
|
ሣ
|
1ኛ ሩብ ዓመት
|
2ኛ ሩብ ዓመት
|
3ኛ ሩብ ዓመት
|
4ኛ ሩብ ዓመት
|
|||||||||||||
ሀ
|
ነ
|
መ
|
ጥ
|
ህ
|
ታ
|
ጥ
|
የ
|
መ
|
ሚ
|
ግ
|
ሰ
|
|||||||
5
|
የቀበሌ ትስቦና ወመህን አፈፃፀማቸውን ለመገንባት በአዲስ መልክ ማደራጀት ሃላፊነታቸውንና
ተግባራታቸውን ማሳወቅ
|
በቁጥር
|
1
|
1
|
||||||||||||||
6
|
ለህ/ሰቡ ፤ለመ/ራን፤ ለወመህና ፤ተስቦ
ለተማሪዎች የእቅድ ማስተዋወቅ ስራ በመስራት በሁሉም ዘንድ ተነሳሽነት በመፍጠር ተልኮ መስጠት
|
በቁጥር
|
1
|
1
|
||||||||||||||
7
|
ለድርጅት አባሉ የእቅድን ኦሬንቴሽን መስጠት
|
በቁጥር
|
1
|
1
|
||||||||||||||
8
|
የአባሉን የመፈፀም አቅም በመገንባት ተልእኮዎችን ቆጥሮ መስጠት መቀበል
|
በቁጥር
|
1
|
1
|
||||||||||||||
9
|
የተማሪዎች ህዋስን ማጠናከርናየአባላትን የጠራ መረጃ መያዝ
|
በቁጥር
|
10
|
1
|
1
|
1
|
1
|
1
|
1
|
1
|
1
|
1
|
1
|
|||||
10
|
መምህራንን በልማት ቡድን በ1፡5 በወመህ በህዋስ ፤በድፓርትመንት፣በኮሚቴ
ማደራጀት
|
በቁጥር
|
1
|
1
|
||||||||||||||
11
|
ተማሪዎችን በክበባትና ኮሚቴዎች፤ በህዋሳት
በ ልማት ቡድን በክፍል ውስጥ በ1፡5 አደረጃጀት፤ በአለቆች
ህብረት ፤የጎበዝ ተማሪዎች ህብረት የተማሪዎች ፤ፓርላማ በማደራጀት ወደ ስራ ማስገባት
|
በ%
|
1
|
1
|
||||||||||||||
12
|
ü የተሰባበሩ የውሃ ቦኖችን ማስጠገንና ተማሪውንና ት/ቤቱ ተጠቃሚ ማድረግ
ü የተበዳደሱ ሰሌዳዎችንና ወንበሮችን መቀየር
ü 35 ኮንፓይንድ ዲስኮችን ማሰራት ሌላ 50 ወንበር ማስጠገን
ü የተገነጠሉ በርና መስኮት ማስጠገን
|
በ%
|
100
|
50
|
50
|
|||||||||||||
13
|
በጎልመሶች የተቀናጀ ተግባር ተኮር ትም/ት ላይ ለጎልማሳውና ለአጋር አካላት ግንዛቤ መፍጠር
|
በ%
|
2
|
1
|
1
|
|||||||||||||
የትግበራ ምዕራፍ
|
||||||||||||||||||
ተ.ቁ
|
የሚከናወኑ ተግባራት
|
መለኪያ
|
መጠን
|
የበጀት ምንጪ
|
በጀት
|
የክንውን ወቅት
|
||||||||||||
ብ
|
ሣ
|
1ኛ ሩብ ዓመት
|
2ኛ ሩብ ዓመት
|
3ኛ ሩብ ዓመት
|
4ኛ ሩብ ዓመት
|
|||||||||||||
ሀ
|
ነ
|
መ
|
ጥ
|
ህ
|
ታ
|
ጥ
|
የ
|
መ
|
ሚ
|
ግ
|
ሰ
|
|||||||
15
|
የትም/ት ሳምንት በደመቀ ሁኔታ በማክበር የአመቱን ት/ት በተነሳሽነት መጀመር
|
በቁጥር
|
1
|
300
|
00
|
1
|
1
|
-
|
||||||||||
16
|
Ø ነባር ተማሪዎች በሙሉ ወደ ት/ቤት እንዲመጡ ማድረግ
Ø እድሜአቸው ለትም/ት የደረሱ ህፃናት ሁሉም ት/ቤት እንዲገቡ ማድረግ
Ø እድሜአቸው ከ4-6 ዓመት የሆናቸውን ህፃናት ወደ ቅ/መደበኛ ማስገባት
|
1
|
1
|
|||||||||||||||
17
|
መ/ራንና ህ/ሰቡ በት/ቤቱ ችግሮች ዙሪያ በማዎያየት ንቅናቄ ውስጥ ማስገባት
|
10
|
1
|
1
|
1
|
1
|
1
|
1
|
1
|
1
|
1
|
1
|
||||||
18
|
ሁሉም ተማሪዎች በእያንዳነዱ የትም/ት አይነት ቢያንስ ከ50%
በላይ እንዲያመጡ ማስቻል
|
%
|
100
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
|||||
19
|
ከ2-4 ክፍል ድረስ ማንበብ፣መፃፍ፣ማስላት የማይችል ተማሪ እንዳይኖር የሚያስችል የማብቃት ስራ
በትኩረት መፈፀም
|
%
|
100
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
|||||
20
|
አዲስ ገቢ ተማሪዎች /1ኛ ክፍል/እስከ ህዳር 30/2008 ዓ.ም ድረስ ማንበብ መፃፍ ማስላት እንዲችሉ
ማድረግ
|
%
|
100
|
30
|
30
|
40
|
||||||||||||
21
|
ሁሉም መምህራን ተሙማ እንድከታተሉና ሙያቸውን እንዲያሻሽሉ ማድረግ
|
%
|
100
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
|||||
22
|
ሁሉም የስነ-ዜጋ ና ስነ-ምግባር መ/ራን እሴቶችን የተላበሱና በስነምግባራቸውም
ለተማሪዎችና መ/ራን አርአያ ሆነው እንዲገኙ ቀጣይነት ያለው ስልጠናና የማብቃት ስራ መስራት
|
%
|
100
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
|||||
23
|
በሁሉም ክፍሎች በአዲሱየስርዓተ ትምህርት ማቴሪያሎች ትምህርቱ እንዲሰጥ ማድረግ
|
%
|
100
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
|||||
ተ.ቁ
|
የሚከናወኑ ተግባራት
|
መለኪያ
|
መጠን
|
የበጀት ምንጪ
|
በጀት
|
የክንውን ወቅት
|
||||||||||||
ብ
|
ሣ
|
1ኛ ሩብ ዓመት
|
2ኛ ሩብ ዓመት
|
3ኛ ሩብ ዓመት
|
4ኛ ሩብ ዓመት
|
|||||||||||||
ሀ
|
ነ
|
መ
|
ጥ
|
ህ
|
ታ
|
ጥ
|
የ
|
መ
|
ሚ
|
ግ
|
ሰ
|
|||||||
24
|
*
የቅድመ መደበኛ ት/ትን 50% ማድረስ
*
ንጥር ቀብለን 100% ጥቅል ተሳትፎን
100% ማድረስ
|
%
|
100
|
90
|
10
|
|||||||||||||
25
|
*
የማቋረጥ መጠንን ከ1% በታች ዝቅ ማድረግ
*
ጎልማሶችን በ4 ጣቢያዎች እንዲማሩ ማድረግ
|
%
|
100
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
|||||
26
|
በተግባር ወቅት የሚከሰቱ አፍራሽና አደናቀፊ አዝማሚያዎችን መለየት ማጋለጥና መተጋል ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ እንድመጡ
ማድረግ
|
%
|
100
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
|||||
27
|
ምርጥ ተሞክሮን እየቀመሩ ትም/ት መውሰድና በሁሉም ትም/ት ክፍሎች
ማስፋት ተግባራዊ ማድረግ
|
%
|
100
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
|||||
28
|
*
የመ/ራን የልማት ሰራዊት የተማሪዎች የ1፡5 አደራጃጀት የብሎክ አደረጃጀት ክበባት፣ትም/ት ክፍሎችን
በቁልፍና በአብያት ተግባራት ለተገለፀው ተግባራት ማስፈፀሚያነት መጠቀም፡፡
*
ሁሉም አደረጃጀቶች እቅድ እንዲኖራቸውና በእቅድ እንዲመሩ ማድረግ አፈፃፀማቸውን መገምገምና ማስተካከል፡፡
|
%
|
100
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
|||||
29
|
*
የተማሪ መፅሀፍትን በጥንቃቄ ለተማሪው
እንዲደርስ ማድረግ
*
የቤተ-ሙከራ ፣የቤተ-መፅሀፍ ተሟልተው
ለተማሪው አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ
|
%
|
100
|
100
|
||||||||||||||
30
|
*
የሬዲዮ ትምህርት በአግባቡ እንድሰጥ ማድረግና በግብዓት መደገፍ
*
የሚኒሚዲያ አገልግሎት በጥራት መጠቀምና የት/ቤቱን ስራ ማስተዋወቅና
ለተማሪዎች መረጃ እንድደርስ ማድረግ
|
%
|
100
|
4000
|
00
|
100
|
||||||||||||
ተ.ቁ
|
የሚከናወኑ ተግባራት
|
መለኪያ
|
መጠን
|
የበጀት ምንጪ
|
በጀት
|
የክንውን ወቅት
|
||||||||||||
ብ
|
ሣ
|
1ኛ ሩብ ዓመት
|
2ኛ ሩብ ዓመት
|
3ኛ ሩብ ዓመት
|
4ኛ ሩብ ዓመት
|
|||||||||||||
ሀም
|
ነሃ
|
መስ
|
ጥቅ
|
ህዳ
|
ታህ
|
ጥር
|
የካ
|
መጋ
|
ሚያ
|
ግን
|
ሰኔ
|
|||||||
31
|
*
በተደራጀው የትም/ት የልማት ሰራዊት ዘወትር
እሮብ በመገኘት ያለውን ሁኔታ መከታተል ችግሩን መለየት መደገፍና
*
የመ/ራን ደረጃ ተቆጥሮ በተሰጠው ስራ
መሰረት በየሳምንቱና በየወሩ ማውጣት
|
%
|
100
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
10
|
|||||
የማጠቃለያ ምዕራፍ
|
||||||||||||||||||
32
|
የ2008ዓ.ም የአጠቃላይ የስራ ግምገማ በማካድ መልካም ትምምህርቶችንና መሻሸል የሚገባቸውን እንዲሁም
ተሞክሮዎችን መለየት
|
ቁጥር
|
2
|
1
|
1
|
|||||||||||||
33
|
ከግባቸው የደረሱ ትምምህርት ክፍሎችን መምህራንን ተማሪዎችን መለየት የገንዘብ የመፀሀፍት የምስክር
ወረቀትነ ሽልማት መሸለምና ማበረታታት
|
ቁጥር
|
2
|
5000
|
00
|
1
|
1
|
|||||||||||
34
|
ሂስና ግለሂስ ከግምገማው በመነሳት ማካሄድና ለር/መ/ራን ለመ/ራን ደረጃና ምደባ መስጠት
|
ቁጥር
|
2
|
1
|
1
|
|||||||||||||
35
|
አፈፃፀማችን የደከሙ ተግባራቶች በዝርዝር መረጃ መያዝና ለቀጣይ የዕቅድ ዝግጅት ግብአት አድርጎ መጠቀም
|
ቁጥር
|
2
|
1
|
1
|
|||||||||||||
37
|
ዝቅተኛ አፈፃፀም ላላቸው የንቁ ደወል ጥሪ የምስክር ወረቀት መስጠት
|
ቁጥር
|
10
|
1
|
1
|
1
|
1
|
1
|
1
|
1
|
1
|
1
|
1
|
የላልይበላ የመ/ደ/ሙ/ሳ/ት/ቤት የ2008ዓ.ም የሰው ኃይልና የህብረተሰብ
ተሳትፎ እቅድ
የአስተዳደር ሰራተኛ እቅድ ልዩ ፍላጎት ተማሪዎች
የትምህርት ደረጃ
|
ወንድ
|
ሴት
|
ድምር
|
10ኛ ክፍልና በታች
|
5
|
1
|
6
|
ሰርቲፊኬት
|
0
|
1
|
1
|
ድፕሎማ
|
3
|
5
|
8
|
ድምር
|
8
|
7
|
15
|
የጉዳቱ ዓይነት
|
ወንድ
|
ሴት
|
ድምር
|
ማየት
|
2
|
1
|
3
|
መስማት
|
5
|
8
|
13
|
አዕምሮ
|
4
|
11
|
15
|
እንቅስቃሴ
|
1
|
2
|
3
|
ድምር
|
12
|
22
|
34
|
ደረጃ
|
ወንድ
|
ሴት
|
ድምር
|
ደረጃ 1
|
40
|
38
|
78
|
ደረጃ 2
|
21
|
25
|
46
|
ድምር
|
61
|
63
|
124
|
አመቻች
|
0
|
3
|
3
|
የመምህራን ጥቅል እቅድ
የቅድመ መደበኛ ህጻናት
የትምህርት ደረጃ
|
ወንድ
|
ሴት
|
ድምር
|
ሰርቲፊኬት
|
5
|
5
|
10
|
ድፕሎማ
|
16
|
34
|
50
|
ድግሪ
|
2
|
1
|
3
|
ድምር
|
23
|
40
|
63
|
መደበኛ ተማሪ እቅድ በክፍል
ደረጃ
የክፍል ደረጃ
|
ወንድ
|
ሴት
|
ድምር
|
ንጥር
|
77
|
50
|
127
|
1ኛ
|
115
|
135
|
250
|
2ኛ
|
113
|
125
|
238
|
3ኛ
|
115
|
116
|
231
|
4ኛ
|
117
|
146
|
263
|
1-4ኛ
|
460
|
522
|
982
|
5ኛ
|
120
|
135
|
255
|
6ኛ
|
117
|
139
|
256
|
7ኛ
|
97
|
130
|
227
|
8ኛ
|
130
|
144
|
274
|
5-8ኛ
|
464
|
548
|
1012
|
1-8ኛ
|
924
|
1070
|
1994
|
የተቀናጀ
ተግባር ተኮር ትምህርት እቅድ
ደረጃ
|
ወንድ
|
ሴት
|
ድምር
|
ደረጃ 1
|
170
|
272
|
442
|
ደረጃ 2
|
27
|
41
|
68
|
ድምር
|
197
|
313
|
510
|
አመቻች
|
2
|
2
|
4
|
የ2008 ዓ.ም የህብረተሰብ ተሳትፎ እቅድ
በጉልበት
|
በቁሳቁስ
|
በጥሬ ገንዘብ
|
ድምር
|
135000
|
69500
|
72600
|
277100
|
አጠቃሎ (ABSTRACT)
ይህ የላልይበላ የመ/ደ/ሙ/ሳ/ት/ቤት የ2008ዓ.ም
የት/ቤት ማሻሻያ እቅድ ከ2007ዓ.ም እቅድ ግምገማ በመነሳት የት/ቤታችን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ወደ ተሸለ ደረጃ ለማድረስ
መሪ በመሆን ያገለግላል፡፡ ለዚህም ነው በት/ቤት ማሻሻያ መርሃ ግብር ስር የሚገኑትን 4ቱን ዶሜኖች በዝርዝር በመገምገምና እንድሁም
የአጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ መርሃ ግብሮችን በማካተት እቅዱ ሊታቀድ የቻለው፡፡ በዚህም መሰረት ይህ የት/ቤት ማሻሻያ
እቅድ በውስጡ፡-
Ø
አጠቃላይ
የት/ቤቱን ታሪካዊ አመሰራረትና አቀማመጥ
Ø
የት/ቤታችን
ራዕይ ተልኮ እሴቶች የአሰራር መርሆዎች
Ø
የት/በታችን
ምቹ ሁኔታዎችና ፈታኝ ሁኔታዎች
Ø
የእቅዱ
መነሻ ሁኔታዎችና የሁኔታ ትንታና
Ø
የእቅድ
አላማ ግብና ዝርዝር ተግባራት
Ø
የእቅዱ
የድርጊት መርሃ ግብር
Ø
የት/ቤቱ
አጠቃላይ ፊዚካል እቅድ ( የሰው ሃይልና የህብረተሰብ ተሳትፎ) በዝርዝር የያዘ ሲሆን ለእያንዳንዱ የእቅድ ተግባራት የሚከናወኑበት
ስልትና በማን መቼ እንደሚከናወኑ በዝርዝር አስቀምጠናል፡፡
No comments:
Post a Comment